የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረበት ጊዜ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዚልፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር፤ የእነርሱንም ክፋት ነገር ዮሴፍ ወደ አባታቸው አመጣ።
ማቴዎስ 18:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባልንጀሮቹ ባርያዎችም ያደረገውን ሁሉ አይተው እጅግ አዘኑ፤ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሆነውን ነገር ያዩ ሌሎች አገልጋዮችም በጣም ዐዘኑ፤ ሄደውም ሁኔታውን በሙሉ ለጌታቸው ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደርሱ ያሉ ሌሎች የሥራ ጓደኞቹ ይህን ባዩ ጊዜ እጅግ አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፤ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ። |
የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረበት ጊዜ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዚልፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር፤ የእነርሱንም ክፋት ነገር ዮሴፍ ወደ አባታቸው አመጣ።
አገልጋዩም መልሶ ይህንን ለጌታው ነገረው። በዚያን ጊዜ ባለቤቱ ተቆጥቶ አገልጋዩን ‘ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች መንገዶች ውጣ፤ ድሆችንና ጉንድሾችን ና ዐይነ ስውሮችንና አንካሶችንም ወደዚህ አስገባ፤’ አለው።
ለዚህ ደካሞች መስለን መቅረባችንን በኀፍረት እናገራለሁ። ነገር ግን በሞኝነት እላለሁ፤ ማንም ለመመካት በሚደፍርበት እኔ የምደፍርበት አለኝ።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።