ማቴዎስ 10:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰዎች ተጠንቀቁ፥ ምክንያቱም ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ይዘው ለፍርድ ወደ ሸንጎ ያቀርቧችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፏችኋል፤ ስለዚህ ከእነርሱ ተጠንቀቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ወደ ፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራባቸውም ይገርፉአችኋል፤ ስለዚህ ከሰዎች ተጠንቀቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ |
ስለዚህ እነሆ እኔ ነቢያትን፥ ጥበበኞችና ጻፎችን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ ትሰቅላላችሁም፥ ከእነርሱም አንዳንዶቹን በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዱአቸዋላችሁ፤
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራብ ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
በምኵራብም ሁሉ ብዙ ጊዜ እየቀጣሁ ይሰድቡት ዘንድ ግድ አልኋቸው፤ ያለ ልክ ስቆጣባቸውም እስከ ውጭ አገር ከተማዎች ድረስ እንኳ አሳድድ ነበር።
በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ።