ማርቆስ 5:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ወዲያውኑ ኃይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐውቆ፤ ወደ ሕዝቡ ዞሮ፥ “ልብሴን የነካ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውኑ ኢየሱስ፣ ኀይል ከርሱ እንደ ወጣ ዐውቆ፤ ወደ ሕዝቡ ዘወር በማለት፣ “ልብሴን የነካው ማን ነው?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ወዲያውኑ ኀይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐወቀ፤ ወደ ሕዝቡም ዘወር ብሎ፦ “ልብሴን የነካ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ “ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ፦ ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው? አለ። |
እንዲህም ሆነ፤ አንድ ቀን ሲያስተምር ሳለ ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮች ሁሉ ከኢየሩሳሌምም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ የሚፈውስበትም የጌታ ኃይል ከእርሱ ጋር ነበረ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።