Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 5:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የሚፈሰው ደሟ ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሥቃይዋ እንደዳነች በሰውነቷ ታወቃት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሥቃይዋ መገላገሏም በሰውነቷ ታወቃት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የሚፈሰው ደምዋም ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሕመምዋም እንደ ዳነች በሰውነትዋ ተሰማት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ፤ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 5:29
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር ቢመጣ፥ በውርጭ፥ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ ቢትወረር፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥


ጥፋትሽንም ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥


ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከአዘቅትም አዳናቸው።


ልባቸው የተሰበረባቸውን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።


አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።


እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።


“ካህኑም ገብቶ ቢያይ፥ እነሆም፥ ቤቱ ከተመረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይሰፋ፥ ደዌው ስለ ጠፋ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።


ማናቸውም ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርሷም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።


እነሆ ለዐሥራ ሁለት ዓመታት ደም የሚፈስሳት ሴት ከኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤


ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ በሕመም የሚሠቃዩ ሁሉ በእጃቸው ሊነኩት ፈልገው ያጨናንቁት ነበር።


ምክንያቱም፥ “እንደ ምንም ብዬ ልብሱን እንኳ ብነካ ይፈውሰኛል” በማለት ነበር።


እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሺ” አላት።


በዚያች ሰዓት ኢየሱስ ከደዌና ከሚያሠቃይ በሽታ፥ ከክፉዎች መናፍስትም ብዙዎችን ፈወሰ፤ ለብዙ ዐይነ ስውሮችም የማየትን ጸጋ ሰጠ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች