ማርቆስ 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ግን አልፈቀደለትም፤ ይልቁን፥ “ወደ ቤትህ ወደ ዘመዶችህም ሂድ፤ ጌታም ምን ያህል ታላቅ ነገር እንዳደረገልህና ምሕረት እንዳሳየህ ንገራቸው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ አልፈቀደለትም፤ ነገር ግን፣ “ወደ ቤትህ ሂድ፣ ለዘመዶችህም ጌታ ምን ያህል ታላቅ ነገር እንዳደረገልህና ያሳየህን ምሕረት ንገራቸው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን አልፈቀደለትም፤ ነገር ግን፥ “ወደ ቤትህ ሂድና ጌታ ምን ያኽል ታላቅ ነገር እንዳደረገልህና እንዴትስ እንደማረህ ለቤተሰብህ አውራላቸው፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም አልፈቀደለትም፤ ነገር ግን “ወደ ቤትህ ወደ ቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም አልፈቀደለትም፥ ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ በቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው አለው። |
“ወደ ቤትህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ተናገር።” እርሱም በመላው ከተማ ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት እየሰበከ ሄደ።