ማርቆስ 3:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ንብረቱን መዝረፍ የሚችል የለም፤ ያንጊዜ ግን ቤቱን ይዘርፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም የተነሣ አንድ ሰው አስቀድሞ ኀይለኛውን ሰው ሳያስር ወደ ኀይለኛው ሰው ቤት ሊገባና ንብረቱን ሊዘርፍ አይችልም፤ ቤቱን መዝረፍ የሚቻለው ኀይለኛውን ሰው ሲያስር ብቻ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንዲሁም ወደ አንድ ኀይለኛ ሰው ቤት ገብቶ አስቀድሞ ኀይለኛውን ሰው ሳያስር ንብረቱን መዝረፍ የሚችል የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፤ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። |
በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።
ወይስ አንድ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ንብረቱን እንዴት መዝረፍ ይችላል? ካሰረው በኋላ ግን ቤቱን ይዘርፋል።
እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ፥ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ እርሱም ዲያብሎስ ነው።
ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ጀምሮ ኃጢአትን ይሠራል። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።