ሉቃስ 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄሮድስም፦ “እኔ የዮሐንስን ራስ አስቈረጥሁ፤ ታዲያ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ይህ ማን ነው?” አለ። ሊያየውም ይሻ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሄሮድስም፣ “መጥምቁ ዮሐንስን እኔው ራሴ ዐንገቱን አስቈርጬው ሞቷል፤ ታዲያ፣ ስለ እርሱ እንዲህ ሲወራ የምሰማው ይህ ሰው ማነው?” አለ፤ በዐይኑም ሊያየው ይሻ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄሮድስም በበኩሉ “እኔ የዮሐንስን ራስ አስቈርጬ ነበር፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ ነገር ያደርጋል እየተባለ የሚነገርለት እርሱ ማን ነው?” ይል ነበር። ሊያየውም ይፈልግ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄሮድስም፥ “እኔ የዮሐንስን ራስ አስቈረጥሁ፤ እንግዲህ ስለ እርሱ ሲወራ የምሰማው ይህ ማነው?” አለ፤ ሊያየውም ይሻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄሮድስም፦ ዮሐንስንስ እኔ ራሱን አስቈረጥሁት፤ ይህ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ማን ነው? አለ። ሊያየውም ይሻ ነበር። |
ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፤ ተአምር ሲሠራ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር።