Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሄሮድስም በበኩሉ “እኔ የዮሐንስን ራስ አስቈርጬ ነበር፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ ነገር ያደርጋል እየተባለ የሚነገርለት እርሱ ማን ነው?” ይል ነበር። ሊያየውም ይፈልግ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሄሮድስም፣ “መጥምቁ ዮሐንስን እኔው ራሴ ዐንገቱን አስቈርጬው ሞቷል፤ ታዲያ፣ ስለ እርሱ እንዲህ ሲወራ የምሰማው ይህ ሰው ማነው?” አለ፤ በዐይኑም ሊያየው ይሻ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሄሮድስም፦ “እኔ የዮሐንስን ራስ አስቈረጥሁ፤ ታዲያ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ይህ ማን ነው?” አለ። ሊያየውም ይሻ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሄሮ​ድ​ስም፥ “እኔ የዮ​ሐ​ን​ስን ራስ አስ​ቈ​ረ​ጥሁ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ እርሱ ሲወራ የም​ሰ​ማው ይህ ማነው?” አለ፤ ሊያ​የ​ውም ይሻ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሄሮድስም፦ ዮሐንስንስ እኔ ራሱን አስቈረጥሁት፤ ይህ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ማን ነው? አለ። ሊያየውም ይሻ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:9
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም ሄሮድስ ምንም በደል ስላላገኘበት ወደ እኛ መልሶ ልኮታል፤ እንግዲህ ይህ ሰው ለሞት የሚያደርሰው ምንም ነገር አላደረገም።


ሄሮድስ ኢየሱስን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ ኢየሱስ ይሰማ ነበርና ሊያየው ብዙ ጊዜ ይመኝ ነበር፤ እንዲሁም ኢየሱስ ተአምር ሲያደርግ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች