ሉቃስ 9:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎችም “ኤልያስ ተገለጠ፤” ሌሎችም “ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል፤” ይሉ ስለ ነበር ግራ ተጋባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎች ኤልያስ እንደ ተገለጠ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሙታን እንደ ተነሣ ይናገሩ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም አንዳንዶቹ “ነቢዩ ኤልያስ ተመልሶ መጥቶአል፤” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሞት ተነሥቶአል፤” ይሉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስ ተገለጠ የሚሉም ነበሩ፤ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል የሚሉም ነበሩና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስ ከሙታን ተነሣ፥ ሌሎችም፦ ኤልያስ ተገለጠ፥ ሌሎችም፦ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይሉ ስለ ነበሩ አመነታ። |