በማግስቱም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኘው።
በማግስቱም ከተራራው ከወረዱ በኋላ፣ ብዙ ሕዝብ መጥቶ ኢየሱስን አገኘው።
በማግስቱ ኢየሱስና ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ከተራራው በወረዱ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን ተገናኙት።
በሁለተኛውም ቀን ከተራራው ወረዱ፤ ብዙ ሕዝብም ተቀበሉት።
በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።
እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ “መምህር ሆይ! ለእኔ ብቸኛ ልጄ ነውና፥ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።