ሉቃስ 7:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ በእርግጥ ከሌሎች ሥልጣናት በታች የተሾምሁ ሰው ነኝ፤ ከእኔም በታች ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱንም ‘ሂድ!’ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ብለው ይመጣል፤ ኣገልጋዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ብለው ያደርጋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ራሴ የበላይ አለቃ አለኝ፤ ከበታቼም የማዝዛቸው ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን፣ ‘ሂድ’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን፣ ‘ና’ ስለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም፣ ‘ይህን አድርግ’ ስለው ያደርጋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ራሴ ለባለ ሥልጣኖች ታዛዥ ስሆን ከእኔ በታች የማዛቸው ወታደሮች አሉኝ። ስለዚህ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታደሮችም አሉኝ፤ አንዱን ሂድ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ና ብለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም እንዲህ አድርግ ብለው ያደርጋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ደግሞ ከሌሎች በታች የምገዛ ሰው ነኝ፥ ከእኔም በታች ወታደሮች አሉኝ፥ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም፦ ና ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል። |
ኢየሱስም ይህንን ሰምቶ በእርሱ ተደነቀ፤ ዘወርም ብሎ ለተከተሉት ሕዝብ እንዲህ አለ፦ “እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።”
ከመቶ አለቆቹም ሁለት ጠርቶ “ወደ ቂሣርያ ይሄዱ ዘንድ ሁለት መቶ ወታደሮችንና ሰባ ፈረሰኞችን ሁለት መቶም ባለ ጦር መሣሪያዎችን ከሌሊቱ በሦስተኛው ሰዓት አዘጋጁ፤” አላቸው።
ስለ እርሱም ወደ ጌታዬ የምጽፈው እርግጥ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን ነገር አገኝ ዘንድ በፊታችሁ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ!በፊትህ አመጣሁት፤
ባርያዎች ሆይ! ሰውን ደስ ለማሰኘት ስትሉ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ፤ ነገር ግን በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ታዘዙ።