ሉቃስ 7:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጉርዋም አበሰች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፤ “ይህችን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ አንተ ለእግሮቼ ውሃ እንኳ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን እግሮቼን በእንባዋ እያራሰች በጠጕሯ አበሰች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሴትዮዋ መለስ ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ስገባ አንተ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን በእንባዋ አጥባ በጠጒርዋ አበሰችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፥ “ይህቺን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእግሮች ውኃ ስንኳ አልሰጠኸኝም፤ እርስዋ ግን አልቅሳ በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጕርዋም አበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች። |
“ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባርያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፥ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፦ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።
ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው። የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው።
ከዚያም ዳዊት ኦርዮንን፥ “በል እንግዲህ ወደ ቤትህ ወርደህ እግርህን ታጠብ” አለው። ኦርዮን ከቤተ መንግሥት ተሰናብቶ ወጣ፤ ንጉሡም የምግብ ስጦታ ላከለት።
በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ፥ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፤ በራስ ጠጉርዋም ታብሰው፥ እግሩንም ትስመው፥ ሽቶም ትቀባው ነበረች።
እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
እርሷም ተነሥታ በግምባሯ በመደፋት እጅ ከነሣች በኋላ፥ “እነሆ፤ እኔ አገልጋይህ አንተን ለማገልገል፥ የጌታዬንም አገልጋዮች እግር ለማጠብ ዝግጁ ነኝ” አለች።