እርሱም “በልጁ ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ለመስጠት እንዳልሳሳህ እነሆ አየሁ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ” አለ።
ሉቃስ 7:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ አንድ የሞተ ሰው ተሸክመው እያወጡ ነበር፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ነበረ፤ እርሷም መበለት ነበረች፤ የከተማይቱም ብዙ ሕዝብ ከእርሷ ጋር አብረው ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ከተማዋ መግቢያ በር ሲደርስም፣ እነሆ፤ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው ከከተማዋ ወጡ፤ ሟቹም ለእናቱ አንድ ልጅ ብቻ ነበር፤ እናቱም መበለት ነበረች፤ ብዙ የከተማውም ሕዝብ ከርሷ ጋራ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ከተማው በር በደረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያንዲት መበለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳውን ተሸክመው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸውም ለእናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙዎችም የከተማ ሰዎች አብረዋት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ የሞተ ሰው ተሸክመው አወጡ፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ልጅ ነበረ፥ እርስዋም መበለት ነበረች፥ ብዙም የከተማ ሕዝብ ከእርስዋ ጋር አብረው ነበሩ። |
እርሱም “በልጁ ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ለመስጠት እንዳልሳሳህ እነሆ አየሁ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ” አለ።
እግዚአብሔርም፥ “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፥ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋልኝ” አለው።
እነሆ ዘመዶቼ ሁሉ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው፥ ‘ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፥ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለን’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን በማጥፋት፥ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”
እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ምንም እንጀራ እንደሌለኝ በአምላክህ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ፤ በዱቄት ዕቃዬ ውስጥ ካለችው ከአንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮዬ ውስጥ ካለችው ከጥቂት የወይራ ዘይት በቀር ምንም የለኝም፤ ወደዚህ የመጣሁት ትንሽ እንጨት ለቃቅሜ ወደ ቤቴ በመመለስ ይህችኑ ያለችኝን ትንሽ ዱቄት ለልጄና ለእኔ ለመጋገር ነው፤ ይህችም የመጨረሻ ምግባችን ናት፤ ከዚያም በኋላ በራብ ከመሞት አንተርፍም።”
እርሷም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።
“እንግዲህ አሁን ከዚህ ተነሥተህ ሂድና በሲዶና በምትገኘው በስራጵታ ከተማ ተቀመጥ፤ እነሆ በዚያ የምትኖር አንዲት መበለት እንድትመግብህ አዝዣለሁ” አለው።
ኤልሳዕም “በመጪው ዓመት ልክ ይህን ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፦ “አይደለም! ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ የማይፈጸም የተስፋ ቃል አትንገረኝ!” አለችው።
በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርሷም ለመሞት እያጣጣረች ነበር። ሲሄድም ሕዝቡ በዙርያው እየተጋፉት ያጨናንቁት ነበር።
ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነት አወጡት፤ መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ፥ “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”