Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 17:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ኤልያስ ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ በመስጠት “ተመልከቺ፤ እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል!” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከዚያም ኤልያስ ልጁን አስነሥቶ ከሰገነቱ ወደ ምድር ቤት አወረደው፤ ለእናቱም “ልጅሽ ይኸውልሽ፤ ድኖልሻል!” ብሎ ሰጣት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ኤልያስ ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ በመስጠት “ተመልከቺ፤ እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል!” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ኤል​ያ​ስም ብላ​ቴ​ና​ውን ይዞ ከሰ​ገ​ነቱ ወደ ቤት አወ​ረ​ደው፥ ለእ​ና​ቱም ሰጣት፥ “እነሆ፥ ተመ​ል​ከች ልጅሽ ድኖ​አል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ኤልያስም ብላቴናውን ይዞ ከሰገነቱ ወደ ቤት አወረደው፤ ኤልያስም “እነሆ፥ ልጅሽ በሕይወት ይኖራል፤” ብሎ ለእናቱ ሰጣት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 17:23
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም የኤልያስን ጸሎት ሰማ፤ የልጁም እስትንፋስ እንደገና ተመልሶለት ዳነ።


ሴትዮዋም “እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና በአፍህ ያለው የጌታ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅሁ!” ስትል መለሰችለት።


የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ፥ ይናገርም ጀመረ፤ ኢየሱስም ጐልማሳውን ለእናቱ ሰጣት።


እርሱም ሲወርድ ሳለ አገልጋዮቹ ተገናኙትና “ብላቴናህ በሕይወት አለ፤” ብለው ነገሩት።


እጁንም ለእርሷ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት።


ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም የሚታደጓቸውን ሳይሹ የሚበልጠውን ትንሣኤ ለማግኘት እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች