ሉቃስ 23:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመዘጋጀት ቀንም ነበረ፤ ሰንበትም እየጀመረ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕለቱ ሰንበት ሊገባ ስለ ነበር፣ የመዘጋጃ ቀን ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው ዓርብ ማታ ለሰንበት ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ቀን የሰንበት መግቢያ ዐርብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመዘጋጀት ቀንም ነበረ፤ ሰንበትም ሊጀምር ነበረ። |
አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ እንዲሁም ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና፥ ሥጋቸው በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።