Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 23:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ያም ቀን የሰ​ን​በት መግ​ቢያ ዐርብ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ዕለቱ ሰንበት ሊገባ ስለ ነበር፣ የመዘጋጃ ቀን ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 የመዘጋጀት ቀንም ነበረ፤ ሰንበትም እየጀመረ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ይህንንም ያደረገው ዓርብ ማታ ለሰንበት ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 የመዘጋጀት ቀንም ነበረ፤ ሰንበትም ሊጀምር ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 23:54
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና


አይ​ሁድ ግን የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበ​ርና፥ የዚ​ያች ሰን​በ​ትም ቀን ታላቅ ናትና “ሥጋ​ቸው በሰ​ን​በት በመ​ስ​ቀል ላይ አይ​ደር” አሉ፤ ጭን ጭና​ቸ​ው​ንም ሰብ​ረው ያወ​ር​ዷ​ቸው ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።


አሁንም በመሸ ጊዜ የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም በዚያ ቀበ​ሩት፤ ለአ​ይ​ሁድ የመ​ሰ​ና​ዳት ቀን ነበ​ርና፤ መቃ​ብ​ሩም ለሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ቅርብ ነበር።


የፋ​ሲ​ካም የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበር፤ ጊዜ​ዉም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላ​ጦ​ስም አይ​ሁ​ድን፥ “እነሆ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ” አላ​ቸው፤


ሥጋ​ው​ንም አው​ርዶ በበ​ፍታ ገነ​ዘው፤ ማንም ባል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት፥ ከድ​ን​ጋ​ይም በተ​ፈ​ለ​ፈለ መቃ​ብር ቀበ​ረው፤ ታላቅ ድን​ጋ​ይም አን​ከ​ባ​ልሎ መቃ​ብ​ሩን ገጥሞ ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች