ሉቃስ 20:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጸሐፍትና የካህናት አለቆችም ይህን ምሳሌ የተናገረው በእነርሱ ላይ መሆኑን ስላወቁ፣ በዚያ ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ ዐውቀው በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያን ጊዜም የካህናት አለቆችና ጻፎች ሊይዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነርሱ እንደ መሰለ ዐውቀዋልና፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። |