| ሉቃስ 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ያን ጊዜም የካህናት አለቆችና ጻፎች ሊይዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነርሱ እንደ መሰለ ዐውቀዋልና፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩአቸው።ምዕራፉን ተመልከት አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ጸሐፍትና የካህናት አለቆችም ይህን ምሳሌ የተናገረው በእነርሱ ላይ መሆኑን ስላወቁ፣ በዚያ ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።ምዕራፉን ተመልከት መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።ምዕራፉን ተመልከት አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ ዐውቀው በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።ምዕራፉን ተመልከት መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።ምዕራፉን ተመልከት |