ሉቃስ 2:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባሉት ነገሮች ይደነቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቱና እናቱም ስለ እርሱ በተነገረው ነገር ተገረሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍና ማርያም ስለ ሕፃኑ በተባለው ነገር ሁሉ ይደነቁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍና እናቱ ግን በእርሱ ላይ ስለሚናገረው ያደንቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር። |
ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ይከተሉት የነበሩትን እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።
ባዩትም ጊዜ እጅግ ተገረሙ፤ እናቱም፦ “ልጄ ሆይ! ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር እኮ፤” አለችው።