ሉቃስ 19:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላውኛውም መጥቶ ‘ጌታ ሆይ! በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌላውም አገልጋይ ቀርቦ እንዲህ አለው፤ ‘ጌታ ሆይ፤ በጨርቅ ጠቅልዬ ያቈየሁት ምናንህ ይኸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሌላውም አገልጋይ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ ‘ጌታዬ ሆይ! የሰጠኸኝ ገንዘብ ይኸውልህ፤ በጨርቅ ቋጥሬ አስቀምጬው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስተኛውም መጥቶ እንዲህ አለው፦ አቤቱ፥ በእኔ ዘንድ የነበረቺው ምናንህ እነኋት፤ በጨርቅ ጠቅልዬ አኑሬአት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌላውም መጥቶ፦ ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ |
ሞቶ የነበረውም ሰው እጆቹና እግሮቹ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ፤ ተዉት፤” አላቸው።
እንዲሁም በራሱ ላይ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ።