ሉቃስ 18:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ! ማረኝ፤” እያለ ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ጮኸ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ዐይነ ስውሩ፥ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” እያለ ጮኸ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድምፁንም ከፍ አድርጎ፥ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ጮኸ። |
“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
ከፊቱ ይሄዱ የነበሩትና ይከተሉት የነበሩት ሕዝብ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”