ሉቃስ 17:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀን እንዲሁ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንደዚሁ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀንም እንዲሁ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ልጅም በሚመጣበት ቀን እንዲሁ ይሆናል፤ አይታወቅምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀን እንዲሁ ይሆናል። |
በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “እስቲ ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድነው?” አሉት።
ኢየሱስም “አንተ አልህ፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥና በሰማይ ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለው።
እንዲሁም እርሱ ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል በሚመጣበት ጊዜ መከራን ለተቀበላችሁት ከእኛ ጋር ዕረፍትን ይሰጣችኋል፤
በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።
ይልቅስ የእርሱ ክብር በሚገለጥበት ጊዜ ደግሞ ደስ ብሎአችሁ ኀሤት እንድታደርጉ የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በሆናችሁበት መጠን ደስ ይበላችሁ።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።