እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
ሉቃስ 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፤’ በሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፣ ‘ከቍጥር የማንገባ ባሮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን ተግባር ፈጽመናል’ በሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም እንዲሁ የታዘዛችሁትን ሁሉ በፈጸማችሁ ጊዜ፥ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ የፈጸምነውም ግዳጃችንን ብቻ ነው’ በሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ እናንተም ያዘዝኋችሁን ሁሉ አድርጋችሁ ‘እኛ ሥራ ፈቶች አገልጋዮች ነን፤ ለመሥራትም የሚገባንን ሠራን’ በሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ። |
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ድምፅህን አልሰሙም በሕግህም አልሄዱም፥ እንዲያደርጉም ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።