ሉቃስ 16:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘እንግዲያውስ፥ አባት ሆይ! ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱም እንዲህ አለ፤ ‘አባት ሆይ፤ እንግዲያውስ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትሰድደው እለምንሃለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታሙም እንዲህ አለ፤ ‘አባት ሆይ፥ እንግዲያውስ እባክህ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እንዲህ አለው፦ ‘አባት አብርሃም ሆይ፥ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ |
አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
ከዚህም ሁሉ በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ማለፍ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል፤’ አለ።