Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 17:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤ ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ። ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤ ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤ ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 17:14
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዝናንተው ተቀምጠዋል፥ እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል።”


የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማን ነው?


የወራታቸውስ ቍጥር ከተቈረጠ፥ ከእነርሱ በኋላ የቤታቸው ደስታ ምን ይሆናቸዋል?


“ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞልቶት ነበር፥ የክፉ ሰው ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።


እነሆ፥ ዘመኖቼን ከእጅ መዳፍ አሳጠርካቸው፥ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ነው።


እነሆ፥ እነዚህ ክፉዎቸ ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ሀብታቸውን ያበዛሉ።


እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት፥ እንደ ተደበቀ ዕንቁም ብትሻት፥


“መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው በእርሻ ውስጥ አግኝቶ መልሶ የሸሸገው የተሰወረ መዝገብ ትመስላለች፤ ከደስታውም ብዛት ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ያንን እርሻ ገዛው።


አብርሃም ግን ‘ልጄ ሆይ! አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም ነገሮችህን እንደተቀበልህ አስብ፤ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል፤ አንተም ትሠቃያለህ።


ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።


ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስላልሆናችሁ ዓለም ይጠላችኋል።


እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳልሆንሁ ሁሉ እነርሱም ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው።


“እናንተ ከታች ናችሁ፤ እኔ ከላይ ነኝ፤እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም።”


በምድርም ላይ በምቾትና በመቀማጠል በመኖር ለዕርድ ቀን እንደሚዘጋጅ ልባችሁን አወፍራችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች