ሉቃስ 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ ምክንያት በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ በእግዚአብሔር መላእክት ዘንድ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት ደስታ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል። |
በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።