ሉቃስ 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጉድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም፣ “ከእናንተ አንዱ፣ ልጁ ወይም በሬው በሰንበት ቀን ጕድጓድ ቢገባበት ፈጥኖ የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ፦ “ከእናንተ በሰንበት ቀን ልጁ ወይም በሬው በጒድጓድ ውስጥ ቢወድቅበት ወዲያውኑ የማያወጣው ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእናንተ በሬው ወይም አህያው በጕድጓድ ውስጥ የወደቀበት አንድ ሰው ቢኖር ዕለቱን በሰንበት ቀን ያነሣው የለምን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው? አላቸው። |