በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ ‘ትኩሳት ይሆናል፥’ ትላላችሁ፤ እንዲሁም ይሆናል።
የደቡብ ነፋስም ከደቡብ በኩል ሲነፍስ፣ ‘ቀኑ ሞቃት ይሆናል’ ትላላችሁ፤ እንደዚያም ይሆናል።
እንዲሁም ነፋስ በስተ ደቡብ በኩል በሚነፍስበት ጊዜ፥ ‘ዛሬ ሙቀት ይሆናል’ ትላላችሁ፤ በእርግጥም ይሆናል።
የአዜብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም ‘ድርቅ ይሆናል፤’ ትላላችሁ እንዲሁም ይሆናል።
በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ፦ ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፥ ይሆንማል።
በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥ ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
እንዲህም አሉት ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑን ድካምና ሐሩር ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው።’
አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤