ሉቃስ 10:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጉዞአቸውም ላይ ሳሉ እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ መንገድ ሲሄዱ፣ ኢየሱስ ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መንገዱን ቀጥሎ ወደ አንዲት መንደር ደረሰ፤ በዚያም ማርታ የምትባል አንዲት ሴት በቤትዋ ተቀበለችው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ሄደው ወደ አንዲት መንደር ገቡ፤ ማርታ የምትባል አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው። |
ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ “ጌታ ሆይ! እኅቴ ብቻዬን እንዳገለግል ስትተወኝ አይገድህምን? እንግዲያውስ እንድታግዘኝ ንገራት፤” አለችው።
እርሷም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፤” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።