ሐዋርያት ሥራ 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እነዚህም ሁሉ ‘ኢየሱስ የሚሉት ሌላ ንጉሥ አለ፤’ እያሉ የቄሣርን ትእዛዝ ይቃወማሉ፤” ብለው ጮኹ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ኢያሶንም በቤቱ ተቀብሏቸዋል፤ እነዚህም ሁሉ፣ ‘ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ’ በማለት የቄሳርን ሕግ የሚጥሱ ናቸው።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ኢያሶንም ተቀብሎአቸዋል፤ ‘ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ’ እያሉም የሮምን ንጉሠ ነገሥት ትእዛዝ ይቃወማሉ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ይህ ኢያሶንም ተቀበላቸው፤ እነርሱም በቄሣር ላይ የወንጀል ሥራ ይሠራሉ፤ ሌላ ሕግንም ያስተምራሉ፤ ኢየሱስም ሌላ ንጉሥ ነው” ይላሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እነዚህም ሁሉ፦ ኢየሱስ የሚሉት ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሣርን ትእዛዝ ይቃወማሉ ብለው ጮኹ። ምዕራፉን ተመልከት |