የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።
ዘሌዋውያን 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእዚህም ነገረሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ጌታ ታመጣለህ፤ ለካህኑም ይሰጣል፥ እርሱም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀውን የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር አምጥተህ ለካህኑ አስረክብ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ይወስደዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእህሉንም መባ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መሥዋዕት አድርገህ ለካህኑ ታስረክበዋለህ፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም ያደረግኸውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ታመጣለህ፤ ወደ ካህኑም ታቀርበዋለህ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም የተደረገውን የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር ታመጣለህ፤ ለካህኑም ይሰጣል፥ እርሱም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል። |
የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።
ካህኑም ከእህሉ ቁርባን መታሰቢያውን አንሥቶ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።