ዘሌዋውያን 17:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ቤት ማናችውም ሰው በሬ ወይም በግ ወይም ፍየል በሰፈሩ ውስጥ ቢያርድ፥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርደው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም እስራኤላዊ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ ወይም ፍየል ቢያርድ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤል ሕዝብ ማናቸውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጪ ቢያርድ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤል ቤት ከመካከላቸውም ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ቢያርድ፥ በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርደው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ቤት ማናችውም ሰው በሬ ወይም በግ ወይም ፍየል ቢያርድ፥ በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርደው፥ |
የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
በጌታ ማደሪያ ፊት ለፊት ለጌታ እንደ ቁርባን አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።
“ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ቤት በመካከላቸውም ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥
እጁንም ለቁርባን ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።