ዘሌዋውያን 11:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ አላቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ |
ኖኅም ለጌታ መሠውያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዓይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።
ስለዚህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ርኩስ ከሆነው ትለያላችሁ፤ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ላይ በሚርመሰመሱ ነፍሳት ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ።
በልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ መልካም የሚሆነው ልባችሁ በጸጋ ቢጸና ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚኖሩትም እንኳን አልተጠቀሙም።