ኢያሱ 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፦ “በእስራኤል አምላክ በጌታ ምለንላቸዋል፤ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ስለማልንላቸው፣ አሁን ጕዳት ልናደርስባቸው አንችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎቹ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብተንላቸዋል፤ ስለዚህም አሁን ጒዳት ልናደርስባቸው አይገባም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ፥ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ምለንላቸዋል፤ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ ምንም አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ምለንላቸዋል፥ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም። |
የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፤ መልካሙ ሰው እንደ ኃጢአተኛው፥ የሚምለው ሰው መሐላን እንደሚፈራው ነው።