ኢያሱ 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች የሾማቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የሾማቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም የመረጣቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች የታወቁትን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች ያዘጋጃቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። |
እንዲህም ብለህ እዘዛቸው፦ ‘በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።’”
ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በጌታ ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል እለፉ፤ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም።