ኢያሱ 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ከተሻገረ በኋላ፣ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ |
ዮርዳኖስንም ተሻገራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ አሞራዊው፥ ፌርዛዊው፥ ከነዓናዊው፥ ኬጢያዊው፥ ጌርጌሳዊው፥ ኤዊያዊው፥ ኢያቡሳዊው ተዋጉአችሁ፤ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋቸው።
እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት በሚሻገሩ ጊዜ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳንስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።