የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 22:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን የርስታችሁ ምድር የረከሰ ቢመስላችሁ የጌታ ማደሪያ ወደሚቀመጥበት ወደ ጌታ ርስት ምድር አልፋችሁ በመካከላችን ውረሱ፤ ከአምላካችንም ከጌታ መሠዊያ ሌላ ለእናንተ መሠዊያ በመሥራታችሁ በጌታና በእኛ ላይ አታምፁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የወረሳችኋት ምድር ረክሳ እንደ ሆነ፣ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ተተከለበት ወደ እግዚአብሔር ምድር መጥታችሁ ከእኛ ጋራ ርስት ተካፈሉ፤ ነገር ግን ከአምላካችን ከእግዚአብሔር መሠዊያ በቀር ሌላ መሠዊያ ሠርታችሁ በእግዚአብሔርም ሆነ በእኛ ላይ አታምፁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሁን ግን ምድራችሁ የረከሰ ቢሆን የእግዚአብሔር ማደሪያ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ምድር ተሻገሩ፤ በመካከላችን ርስት ይኑራችሁ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ወይም በእኛ ላይ አታምፁ።

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን የር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቢያ​ን​ሳ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ወደ​ሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ምድር አል​ፋ​ችሁ ከእኛ ጋር ውረሱ፤ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጭ ለእ​ና​ንተ መሠ​ዊያ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ካዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አት​ተ​ዉት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን የርስታችሁ ምድር የረከሰ ቢመስላችሁ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደሚቀመጥበት ወደ እግዚአብሔር ርስት ምድር አልፋችሁ በመካከላችን ውረሱ፥ ከአምላካችንም ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለእናንተ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔርና በእኛ ላይ አታምፁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 22:19
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ የነበሩ ካህናትና ሌዋውያን ከየአገራቸው ሁሉ ወደ እርሱ መጡ።


አንተ ታመጣቸዋለህ፥ በርስትህም ተራራ ትተክላቸዋለህ፥ ጌታ ሆይ ለማደሪያህ በሠራኸው ስፍራ፥ ጌታ ሆይ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህም በገመድ እየተለካች ትከፋፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም ያለ ጥርጥር ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።’ ”


የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ እነርሱም የምድሪቱ ገዢዎች ሆኑ።


የእስራኤልም ልጆች እንዲህ የሚል ወሬ ሰሙ፦ “እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርተዋል።”