አሞጽ 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህም በገመድ እየተለካች ትከፋፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም ያለ ጥርጥር ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣ ተማርኮ ይሄዳል።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ስለዚህም አሜስያስ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ ‘ሚስትህ በከተማይቱ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በጦርነት ይሞታሉ፤ ርስትህንም ባዕዳን በገመድ ለክተው ይከፋፈሉታል፤ አንተም በአሕዛብ ምድር ትሞታለህ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ያለ ጥርጥር ተማርከው ከአገራቸው ይወሰዳሉ።’ ” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፥ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል። ምዕራፉን ተመልከት |