ኢያሱ 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለቀሩት ለቀዓት ዘሮች ደግሞ ከኤፍሬምና ከዳን ነገድ ጐሣዎች፣ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቀሪው ለቀዓት ጐሣ ከኤፍሬም፥ ከዳንና ከምዕራብ ምናሴ ይዞታዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው። |
በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።
ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።
ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።