Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ለቀሪው ለቀዓት ጐሣ ከኤፍሬም፥ ከዳንና ከምዕራብ ምናሴ ይዞታዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለቀሩት ለቀዓት ዘሮች ደግሞ ከኤፍሬምና ከዳን ነገድ ጐሣዎች፣ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለቀ​ሩ​ትም ለቀ​ዓት ልጆች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ፥ ከዳ​ንም ነገድ፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥር ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 21:5
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሌዊ ልጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ናቸው።


በምዕራብ በኩል ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ግዛት ዐሥር ከተሞች ለቀሩት ለቀዓት ወገን ተሰጡ።


የዓምራም፥ የይጽሃር፥ የኬብሮንና የዑዚኤል ቤተሰቦች በቀዓት ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር፤


የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ጐሣ ወጣ፤ ከሌዊ ነገድ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተከፋፈለ፤ እነዚህም ከተሞች የተወሰዱት ከይሁዳ፥ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ይዞታዎች ነበር፤


ለጌርሾን ጐሣ ከይሳኮር፥ ከአሴር፥ ከንፍታሌምና በባሳን ካለው ከምሥራቅ ምናሴ ግዛት ይዞታዎች ተከፍለው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች