ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ይሪያ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበር፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ተገኙ፤
ኢያሱ 21:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሴቦንና ያዕዜር ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሴቦንንና መሰማርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። |
ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ይሪያ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበር፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ተገኙ፤
አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ! ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፤ አጥፊው በበጋ ፍሬሽና በወይንሽ ላይ መጥቷል።
የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥
የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም ሴዎንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርን፥ ሪባን ድል ነሣቸው።