ኢያሱ 19:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳንም ልጆች ግዛታቸውን መቆጣጠር ባለልቻሉ ጊዜ ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፤ ሌሼም የነበረውን ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የዳን ዘሮች ርስታቸው አልበቃቸውም፣ ወደ ሌሼም ወጥተው አደጋ በመጣል ያዟት፤ ሰዎቹንም በሰይፍ ስለት ፈጅተው ይዞታቸው አደረጓት፤ በዚያው ሰፈሩ፤ ስሟንም ለውጠው በአባታቸው ስም ዳን አሏት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳንም ሕዝብ ይህን ምድር ለመውረስ የማይቻል ሆኖ ባገኙት ጊዜ ወደ ላዪሽ ሄደው አደጋ በመጣል ከተማይቱን ያዙ፤ ሕዝብዋንም ፈጅተው የራሳቸው ይዞታ አደረጉአት፤ በዚያም ሰፈሩ፤ ላዪሽ ትባል የነበረችውን ከተማ ስሟን ለውጠው በቀድሞ አባታቸው ስም ዳን ብለው ጠሩአት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። የዳን ልጆችም በተራራው ላይ የሚያስጨንቋቸው አሞሬዎናውያንን አላስጨነቁአቸውም። አሞሬዎናውያንም ወደ ሸለቆዎች ይወርዱ ዘንድ አልፈቀዱላቸውም። ከእነርሱም ከርስታቸው ዳርቻ አንድ ክፍልን ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፥ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፥ ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት። |