ኢያሱ 19:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መጨረሻውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንበሩ ወደ ራማ ከዞረ በኋላ ወደ ተመሸገው ወደ ጢሮስ ከተማ ታጥፎ ወደ ሖሳ ይመለስና በአክዚብ በኩል ሜድትራኒያን ባሕር ደርሶ ይቆማል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንበሩ እስከ ተመሸገችው እስከ ጢሮስ ከተማ ይደርስና ወደ ራማ ይታጠፋል፤ ከዚያም መመለሻው የሜድትራኒያን ባሕር ሆኖ ወደ ሖሳ ይታጠፋል፤ እርሱም ማሐላብ፥ አክዚብ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞራል፤ ድንበሩም ወደ ኢያሴፍ ይዞራል፤ መውጫውም በሌብና በኮዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፥ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፥ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፥ |
በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልዕክተኞችን፥ የዝግባ ዕንጨት፥ አናጢዎችንና ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፥ ለዳዊት ቤተ መንግሥት ሠሩለት።