ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ሴኬምና መንደሮችዋ ጋዛና መንደሮችዋ ነበሩ፤
ኢያሱ 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ መጨረሻውም ዮርዳኖስ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቍልቍል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያኖሐም ተነሥቶ ወደ ዐጣሮትና ወደ ናዓራት በመዘቅዘቅ ኢያሪኮ ደርሶ መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢያኖክም ወደ መአኮና፥ ወደ አጣሮትም፥ ወደ መንደሮቻቸውም ያልፋል፤ ወደ ኢያሪኮም ይገባል፥ ወደ ዮርዳኖስም ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፥ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ። |
ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ሴኬምና መንደሮችዋ ጋዛና መንደሮችዋ ነበሩ፤
ከዚያም ተነሥቶ ድንበሩ ወደ ባሕሩ በኩል ወጣ፤ በሰሜን በኩል ሚክምታት ይገኝ ነበር፤ ድንበሩም ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናትሴሎ ዞረ፥ ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ፥
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።
በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በጌታ ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ።”