ኢያሱ 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከተዋጊዎቹ ሁሉ ጋር በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጣባቸው፥ በእነርሱም ላይ ጥቃት ፈጸመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱና ሰራዊቱ ሁሉ በድንገት ወደ ማሮን ውሃ መጥተው ወጓቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኢያሱና መላ ሠራዊቱ ዘምተው በሜሮም ድንገተኛ አደጋ ጣሉባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱና ተዋጊዎች ሕዝብም ሁሉ በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጡባቸው፤ በተራራማውም ቦታ ወደቁባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከሰልፈኞቹ ሁሉ ጋር በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጣባቸው፥ ወደቀባቸውም። |
ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ እኔ ሁሉንም እንደሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ።”
ጌታም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፥ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ምጽጳ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ አንድም ሳያስቀሩ መቱአቸው።