ይህን ሲናገር ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
ይህንም እንደ ተናገረ ብዙዎች በርሱ አመኑ።
ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ።
ይህንም በተናገረ ጊዜ ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
ስለዚህ ወደ ማርያም ከመጡት፥ ኢየሱስም ያደረገውን ካዩት ከአይሁድ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤
በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳሉ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤
ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ “ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው፤” አሉ።
ከሕዝቡ ግን ብዙዎች አመኑበትና፥ “ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ ሰው ካደረጋቸው ምልክቶች የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።