Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ “ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው፤” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሰዎቹም ኢየሱስ ያደረገውን ታምራዊ ምልክት ካዩ በኋላ፣ “ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ በርግጥ ይህ ነው” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሰዎቹም ኢየሱስ ያደረገውን ተአምር ባዩ ጊዜ፥ “በእርግጥ ይህ ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው!” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:14
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፥ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።


“የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” አለው።


ሕዝቡም “ይህ በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት የመጣው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” አሉ።


እርሱም “ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ ነው፤


ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸው፤ እግዚአብሔርንም እንዲህ እያሉ አመሰገኑ፦ “ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል!” “እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጐብኝቶአል!”


“እንግዲያውስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን?” ብለው ጠየቁት። “አይደለሁም” አለ። “ነቢዩ ነህን?” “አይደለሁም” ብሎ መለሰ።


እርሷም “አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ እኔ አምናለሁ” አለችው።


ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።


ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደሆንህ አያለሁ።


ሴቲቱ “ክርስቶስ የሚባል መሢሕ እንደሚመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል፤” አለችው።


ሴቲቱንም “አሁን የምናምነው በቃልሽ ምክንያት አይደለም፤ እኛ እራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱ በእውነት የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን፤” ይሉአት ነበር።


በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተለው።


ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።


እንዲህም አሉት፦ “ታዲያ አይተን እንድናምንህ አንተ ምን ዓይነት ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?


ስለዚህ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ በእውነት ነቢዩ ነው፤” አሉ፤


ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት፤’ ያላቸው ሙሴ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች