ዮሐንስ 21:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔርን እንደሚያከብር ሲያመለክት ይህንን ተናገረ። ከዚያም “ተከተለኝ፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ይህን ያለው ጴጥሮስ በምን ዐይነት ሞት እግዚአብሔርን እንደሚያከብረው ለማመልከት ነው። ከዚህ በኋላም፣ “ተከተለኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያለው ጴጥሮስ በምን ዐይነት ሞት እግዚአብሔርን ማክበር እንዳለበት ሲያመለክት ነው፤ ከዚህ በኋላ ጴጥሮስን “ተከተለኝ!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምን ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን ተናገረ፤ ይህንም ብሎ ተከተለኝ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን አለ። ይህንም ብሎ፦ “ተከተለኝ” አለው። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ስለተከተላችሁኝ በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በዓሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ፥ በዓሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይም ትፈርዳላችሁ።
እውነት እውነት እልሃለሁ፤ አንተ ጎልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ቦታ ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፤ ሌላ ሰውም ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል” አለው።
ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በምንም ዓይነት ነገር አላፍርም፤ ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ እንደ ወትሮው እንዲሁ አሁንም በሥጋዬ ይከብራል ብዬ በሙሉ ድፍረት እናገራለሁ።
ሳሙኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “አትፍሩ፤ ይህን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፤ ሆኖም ጌታን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ ጌታን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ።