ዮሐንስ 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደገና ተገለጠላቸው፤ እንዲህም ተገለጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር እንደ ገና ለደቀ መዛሙርቱ ታየ፤ በዚህም ሁኔታ ተገለጠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንደገና ተገለጠ፤ የተገለጠውም እንደሚከተለው ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደገና ተገለጠላቸው፤ እንዲህም ተገለጠላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና ተገለጠላቸው፤ |
ፈጥናችሁ ሂዱና ‘ከሙታን ተነሥቶአል፤ እነሆ ወደ ገሊላ ቀድሞአችሁ ይሄዳል፤ በዚያም ታዩታላችሁ’ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው። እነሆ ነግሬአችኋለሁ።”
ከዚያም ዐሥራ አንዱ በማዕድ ላይ ሳሉ ተገለጠላቸው፤ ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች የነገሯቸውን ስላላመኗቸው፥ አለማመናቸውንና የልባቸውን ድንዳኔ ነቀፈ።
ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።