ዮሐንስ 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም “ጌታ ሆይ! አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ እግሬን ታጥባለህን?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ስምዖን ጴጥሮስ በመጣ ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ፥ “ጌታ ሆይ! አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ስምዖን ጴጥሮስም ደረሰ፤ እርሱም፥ “አቤቱ፥ አንተ እግሬን ታጥበኛለህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን?” አለው። |